Events — Beza International Church

ከፊታችን ባለው በስቅለት በዓል፣ በዮናስ እና በኢየሱስ ታሪክ ስለታየው ወሰን የለሽ የእግዚአብሔር ምሕረት ትርጉም ያለው ምልከታ እንዲኖረን በቤዛ ቤተክርስቲያን ተጋብዛችኋለች።

በስቅለተ አርብ ቀን፣ በኢየሱስ ስቃይ እና ስቅለት ላይ እናተኩራለን— እንዴት ለእኛ ሲል ወደ ስቃይ እና ሞት ጥልቅ እንደ ወረደ። ነገር ግን ዮናስ በአሣ ነባሪ ተውጦ ሦስት ቀን እንዳሳለፈ፣ ኢየሱስም በመቃብር ሦስት ቀን አሳልፏል፤ ሆኖም በድል ተነስቷል! የዮናስ ታሪክ ሁለተኛ እድል እና ከተስፋ መቁረጥ መውጫ መንገድ ወደሚሰጠው የእግዚአብሔር ምሕረት ይጠቁመናል። በኢየሱስ ስቃይ፣ መስዎዓት እና ትንሳኤ፣ ምህረት ለሰው ልጆች ሁሉ እንደተዘረጋ እናያለን፣ ይህም በተስፋ መቁረጥ ጊዜያችንም ቢሆን ተስፋን ያመጣልናል።

የሕይወትን ትርጉም እየፈለግክ፣ ወይም ከእምነት ጋር እየታገልክ፣ ወይም ቤቴ ብለህ የምትጠራው ማህበረሰብ እየፈለግክ ከሆነ ና፣ ነይ። ከስቃይ ጥልቀት የሚወጣውን ጥልቅ ተስፋ እና በክርስቶስ ትንሳኤ የሚመጣውን ህይወት ለመቀበል ኑ። ለመስቀሉ መልዕክት ምላሽ ለመስጠት ኑ።

This Good Friday, Beza Church invites you to join us for a meaningful reflection on God's boundless mercy, seen through the stories of Jonah and Jesus.

We will focus on the suffering and crucifixion of Jesus— how He descended into the depths of pain and death for our sake. But just as Jonah was swallowed by the whale and spent three days before being delivered, Jesus too spent three days in the grave, only to rise again in victory! Jonah’s story points us to the mercy of God, who offers a second chance and a way out of despair. Through Jesus' suffering, sacrifice, and resurrection, we see that mercy extended to all of humanity—bringing hope even in our deepest moments of despair.

Whether you’re searching for meaning, grappling with faith, or seeking a community to call home, you are welcome. Come experience the profound hope that emerges from the depths of suffering and the life that comes through Christ’s resurrection.