Announcements — Beza International Church

☕️ Announcements

1. Easter joint Celebration – Sunday, April 13!

The Ethiopian Evangelical Council would like to celebrate Easter with us this coming Sunday, April 13 at 10:00 AM!

Location: New African Worship Center

This is a special opportunity to gather as one body in Christ to celebrate the resurrection of our Lord Jesus Christ through powerful worship and joyful fellowship.

Come prepared to worship the Lord and experience His presence together with the wider body of believers.

Spread the word and invite others!

#HeIsRisen #EasterCelebration #BezaChurch #OneBodyInChrist

2. Beza Family Day 2025: We will be having a Beza Family Day on May 5 starting from 9am at the Cambridge School located near Goro! It will be a full day program where we will have a time of fellowship and fun with different games that bring together people of all ages. So, if you want to participate in the program, please register at the connection center and make the registration payment. Also select the transportation mode you prefer, using private car or bus and also whether you will be having lunch from the prepare or bringing your own so that we can plan ahead.

3. Ethiopian Good Friday: The Sign of Jonah!

Something’s stirring. 🔥 Watch closely. One spark at a time—until Good Friday. ✨

Date: April 18

#GoodFridayCountdown #SomethingIsComing #HolyWeekPrep #GoodFriday2025

4. Seminar on Singleness, Dating, and Pre-Marriage:

🗓 Date: April 13

⏰ Time: 2:30 PM

Are you single, dating, or preparing for marriage? This seminar is for YOU! Join us as we dive into what you need to know before taking the next big step.

💡 What to Expect:

✨ Practical insights and biblical principles

✨ A safe space to ask honest questions

✨ Engaging discussions and a touch of fun

Don’t miss this opportunity to grow and learn together! Let’s prepare our hearts and minds for the future.

📍 See you there!

5. Beza Creative Team

The Beza Creative Team is recruiting volunteers! Be part of advancing God’s kingdom using your God given gifts. For more info/ to register use this link - bit.ly/BezaCreative

HomeCare: Our small groups meet all over the city during the week and it is where we make friends, be discipled, make disciples. Homecares are where we learn to follow Jesus, through diligent study of God’s word and intentional fellowship with other believers. We invite you to get settled in these intimate and fun settings where you can plug in to Christian community. To join a homecare near you, Please register by texting the Beza phone 0907700007 or call 0920732414 or send a message through our telegram handle @Bezaconnect.

Worship Schedule: worship schedule for our Sunday services:

Amharic service: 8:45 AM - 10:45 AM

English service: 11:15 AM to 1:15 PM

Children’s programs:

Ages 3 – 11 – begins at 11:45 AM

Ages 12 – 14 – begins at 11:45 AM

English High schoolers- begins at 11:45 AM

Discipleship classes: Discipleship classes will be held every Sunday in our classes here at the Tabernacle on 10:00 AM to 11:00 AM.

Prayer Unusual is a going strong. The prayer movement that started at Beza Church is a program where we come and intercede for the nation and for our personal needs. It is being held at the hall dedicated in the basement of the new building for prayer.

Schedule for Prayer Unusual:

Thursday 3 – 5 PM

Friday 1:00PM- 3:00PM Women’s Fellowship

Friday 4 – 7PM (English Program)

Saturday 7 – 8AM Online via Telegram click JOIN on the top of our Telegram Channel (@bezachurch) and join the prayer.

Sunday 7:30 – 8:30AM

☕️ ማስታወቂያ

1. የትንሳኤ የጋራ አምልኮ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ካውንስል የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 5 ከጠዋቱ 4:00 ላይ የትንሣኤን በዓል ከእኛ ጋር ያከብራል!

ቦታ፡ በአዲስ አፍሪካ የአምልኮ ማዕከል

የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤን በአምልኮ እና ክርስትያናዊ በሆነ ህብረት ለማክበር በክርስቶስ እንደ አንድ አካል የመሰብሰብ ልዩ እድል ነው።

ጌታን ከወንድሞች እና እህቶች ጋር በጋራ ለማምለክ ተዘጋጅታችሁ ኑ!

ያላመኑትን እና ሌሎችንም ይጋብዙ!

#ተነሥቷል #የፋሲካ #አከባበር #ቤዛ ቤተክርስቲያን #አንድ አካል በክርስቶስ

2. የቤዛ ቤተሰብ ቀን 2017: ሚያዚያ 27 የቤዛ ቤተሰብ ቀን ከጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ ጎሮ አካባቢ ባለው በካምብሪጅ ት/ቤት ይኖረናል! የሙሉ ቀን ፕሮግራም ሲሆን በዚያም በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የሚያሳትፍ የሕብረትና የመዝናኛ ጊዜ ይኖረናል። ስለሆነም በፕሮግራሙ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ በመገናኛ ማዕከሉ በመመዝገብ መክፈል  ትችላላችሁ። እንዲሁም ወደቦታው ለመሔድ በግል መኪና ወይም በተዘጋጀው ባስ እና ምግብን በተመለከተ ከራሳችን ይዘን እንመጣለን ወይም ከሚዘጋጀው እንገዛለን የሚለውን ለማቀድ እንዲመቸን ምዝገባው ላይ ፃፉልን።

3. ስቅለት: የዮናስ ምልክት፦

አንድ ልዩ 🔥ነገር እያዘጋጀን ነው። እስከ ስቅለት ዓርብ ድረስ አንድ  በ አንድ ወደ አናንተ የምናደርስ  ይሆናል ተከታተሉን አብራቾሁን ሁኑ። ✨

ቀን: ሚያዚያ 10

#የስቅለትበዓል #አዲስነገር #እምነትንበተግባር  #ስቅለት፳፪፭

4. ላላገቡ፣ በመጠናናት ላይ ላሉና የቅድመ-ጋብቻ ሴሚናር፦

🗓 ቀን፡  ሚያዚያ 5

⏰ሰአት፡ 8:30

አላገባችሁም፣ በመጠናናት ላይ ወይም ወደ ጋብቻ መስመር ላይ ናችሁ? እንግዲያውስ ይህ ሴሚናር ለእናንተ ነው። ቀጣዩን ትልቅ እርምጃ ከመውሰዳችሁ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ነገሮችን አብረን እናያለን።

💡 ምን እንጠብቅ፡-

✨ተግባራዊ ግንዛቤዎች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎች

✨ በግልጽነት የምንጠይቅበት

✨ አሳታፊ ውይይቶች እና አዝናኝ ቆይታ ይኖረናል።

አብሮ ለማደግ እና ለመማር ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ! ለወደፊት ልባችንን እና አእምሯችንን እናዘጋጅ።

📍 እዚያው እንገናኝ!

5. የቤዛ የክሬቲቭ ቡድን: የቤዛ የክሬቲቭ ቡድን በጎ ፈቃደኞችን እየመዘገበ ይገኛል! እግዚአብሔር የሰጣችሁን ስጦታዎች በመጠቀም የእግዚአብሔርን መንግሥት በማገልገል አብራችሁን ሁኑ።  ለበለጠ መረጃ/ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ -bit.ly/BezaCreative ወይም ወደ መገናኛ ማእከሉ መሔድ ትችላላችሁ።

ሆምኬር፡- የቤት ውስጥ ሕብረቶቻችን በሳምንቱ ውስጥ በመላ ከተማው ይሰበሰባሉ። እነዚህ ሕብረቶች ወዳጆች የምናፈራበት፣ የምንማከርበትና ደቀ መዛሙርት የምንሆንባቸው ናቸው። ሆምኬሮች የእግዚአብሔርን ቃል በትጋት በማጥናትና ከሌሎች አማኞች ጋር በመተባበር ኢየሱስን መከተል የምንማርበት ነው። ከክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር በምትገናኙባቸው በእነዚህ ቅርበት የተሞላባቸውና አስደሳች ሕብረቶች ውስጥ እንድትተከሉ እንጋብዛችኋለን። በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ሆምኬር ለመቀላቀል በቤዛ ስልክ ቁጥር 0907700007 ወይም በ0920732414 ይደውሉ ወይም በቴሌግራም አድራሻችን @Bezaconnect መልእክት በመላክ ይመዝገቡ።

የአምልኮ ሰዓት:- የእሁድ የአምልኮ ሰዓት፦

የአማርኛ አገልግሎት፦ ከ 2:45 - 4:45

የእንግሊዝኛ አገልግሎት፦ ከ 5:15 - 7:15

የልጆች የሰንበት ትምህርት ፕሮግራም ማስተካከያ፦

ዕድሜያቸው 3 እስከ 11 - በ3:15 ሰዓት ይጀምራል

ዕድሜያቸው 12 እስከ 14 እድሜ - በ2፡45 ሰዓት ይጀምራል

የወጣቶች ፕሮግራም:- የቤዛ የወጣቶች ፕሮግራም ዕድሜያቸው ከ 15-23 ለሆኑ በየሳምንቱ እሁድ በአዲሱ ሕንጻ ቤዝመንት ከ2፡45-4፡45 ይካሄዳል። በየወሩ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 የሙሉ ቀን ፕሮግራም ይኖረናል።

የደቀመዝሙርነት ትምህርት:- የደቀመዝሙርነት ትምህርት እሁድ በታበርናክል ከጠዋቱ 4፡45 እስከ 5፡45 ሰዓት ይካሄዳል። እሁድ መውሰድ የማይችል ማንም ሰው የደቀመዝሙርነት ትምህርት መውሰድ ከፈለገ በሌሎቹ ቀናት ፕሮግራም ስለምናዘጋጅ የምትፈልጉ እባካችሁ በዚህ ቁጥር "0907700007" አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ "@bezaconnect" ይመዝገቡ።

ያልተለመደ ፀሎት ላለፈው ወር በርትቶ እየቀጠለ ነው። በቤዛ ቤተክርስቲያን የተጀመረው የፀሎት እንቅስቃሴ በየሳምንቱ እየቀጠለ ስለሆነ ይምጡና ለሃገራችንና ለተለያዩ ጉዳዮች ማልዱ። በአዲሱ ህንፃ ምድር ቤት ለፀሎት በተዘጋጀው አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ ነው።

ያልተለመደ ፀሎት መርሃ-ግብር፦

ሐሙስ - ክቀኑ 9፡00- 11:00 ሰዓት

ዓርብ - ከቀኑ 7:00- 9:00 ሰዓት (የእህቶች ፕሮግራም)

ዓርብ - ከቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት (የእንግሊዘኛ ፕሮግራም)

ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰዓት-2 ሰዓት በቴሌግራም (ለመግባት በቴሌግራም ቻናላችን (@bezachurch) ከላይ JOIN የሚለውን በመጫን በቀላሉ ፀሎቱን መቀላቀል ትችላላችሁ።)

እሁድ - ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት – 2:30 ሰዓት